መድረክ ነገ ሐምሌ 14 በመቀሌ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ በመኪና ሲቀሰቅሱ የነበሩት የአረና ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ህሺ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀኔ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ በህገወጥ መንገድ መታሰራቸውን የአረና ፓርቲ ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡ ፓርቲው ጨምሮ እንዳስታወቀው ለነገው ስብሰባ ቅስቀሳ እንዳይደረግ የክልሉ መንግስት ሀላፊዎች ክልከላ ቢያደርጉም በነገው እለት ስብሰባው ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በመቀሌ ከተማ ማጋጃ ቤት አዳራሽ ውስጥ ይደረጋል፡፡
↧