Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

በ5 አመቱ እቅድ መጠናቀቅ ያለበት የባቡር ግንባታ፣ ከአንድ በመቶ በታች ብቻ ነው የተጠናቀቀው

$
0
0

የበርካታ የአገዛዙ ባለስልጣናት የግል ቢዝነሶችና ፎቆች በፍጥነትና በጥራት እየተጠናቀቁ ባለብት በአሁኑ ወቅት፣ በ2002 ዓ.ም ለሕዝብ ይፋ ከሆነውና ላለፉት በርካታ አመታት በኢቲቪ ሲነገርለት ከቆየው፣ የአምስት አመቱ የእድገትና የትራስፎርሜሽን እቅዶ ዉስጥ በዋናነት ከሚጠቀሱት ሁለቱ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ፣ በአምስት ኮሪደሮች የታቀደው የባቡር ግንባታ መሆኑ ይታወቃል።

ከታቀደው የ2300 ኪሎሜተር የባቡር መስምር ፣ ከመቶ ኪሎሜትር በላይ እንዳልተሰራ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የፓርላማ አባል የገለጹ ሲሆን፣ ሙሉ ለሙሉ በዚህ ዓመት መጠናቀቅ የነበረበት ፕሮጀክት፣ አንድ ከመቶ ያነሰ ብቻ እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ተችሏል።
“በአራት ኮሪደሮች ለመስራት ካቀድነው ዉስጥ 1500 ኪሎሜትር የሚሆን፣ በሁለት ኮሪደሮች ሥራ መጀመራችን የሚታወቅ ነው” ሲሉ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሥራ እየተሰራ እንደሆነ በመግለጽ እዉነቱን ከመናገር ተቆጥበዋል። ድርጅታቸው ለሕዝብ የገባዉን ቃል አለመጠበቁን አምነው ከመቀበልና፣ ብቃት፣ ጥራት፣ ተጠያቂነትና ግልጽነት ባለው መልኩ ፕሮጀክቶቹ እንዲጠናቀቁ ሁሉንም ዜጎችን ባሳተፈ ሁኔታ መሻሻሎችንና ለዉጦችን ለማድረግ ፍቃደኛ መሆናቸውን ከመግለጽ ይልቅ፣ ሌሎችን መክሰሱን መርጠዋል።
የታቀደው የባቡር ግንባታ አቶ ኃይለማርያም እንዳሉት በአራት ኮሪድሮች ሳይሆን ፣ ከአዲስ አበባ – ወይጦ፣ ከአዲስ አበባ – በደሌ፣ ከአዋሽ – ወልዲያ – ከመቀሌ ታጁራና ከአዲስ አበባ – ጅቡቲ ናቸው ያሉ አምስት ክሪደሮች መሆናቸውም ይታወቃል።

“Presenting a ten-month performance report on Tuesday to the House of Peoples’ Representatives, the Minister of Transport, Workneh Gebeyehu, said that the Ethiopian Railway Corporation was not able to embark on the construction of Awash-Woldiya (Hara Gebeya), Woldiya (Hara Gebya)-Mekelle and Woldiya (Hara Gebya)-Tajura railway projects.” ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ከሶስት ወራት መዘገቡ ይታወሳል።

“According to him, 40 percent of the Addis Ababa-Meiso-Dewele railway line is completed. He also claims that 71 percent of the Addis Ababa light railway line project is finalized. However, sources close to the project reject the performance repot presented by the minister. These sources said that only 40 percent of the work on the Addis Ababa light railway project was done so far.” ሲልም ሪፖርተር በወቅቱ የባቡር ግንባታዉን በተመለከተ ብዙ እንዳልተሰራ ለአንባቢያኑ አትቷል።
አቶ ኃይለማሪያም ለአቶ ግርማ ሰይፉ የመለሱት መለስ፣ ሪፖርተር ከዘገበው፣ የርሳቸው ካቢኔ አባል የሆኑት አቶ ገበየሁ ወርቅነህም በፓርላማ ከተናገሩት ጋር የማይጠጣም እንደሆነ ለማየት ይቻላል።

http://satenaw.com/less-1-planned-2300-km-train-projects-completed-gk/


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>