Quantcast
Channel: Abugida Ethiopian American Amharic Web Page
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

ሚሊዮኖች ድምጽ – 2007 በቃ የምንልበት አመት ነው

$
0
0

የምርጫ አመት ነው። ነጻ ጋዜጦጭ በሙሉ ተዘግተዋል። አገዛዙ በሕዝብና በመንግስት ገንዘብ በየተቋማቱና መስሪያ ቤቶች ስብሰባ እየጠራ ፣ በኢቲቪ ህዝቡን የሚያደነቁረው አንሶት፣ እንደገና በስብሰባ ዜጎችን እያደነቆረ ነው።

advertisement
ኢትዮጵያዊያን የዲሞክራሲያዊ እና ሰብአዊ መብታቸው ተረግጦ በግድ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረጉ ናቸው። አንዳንዶች “ዉሸት ነው። ኢሕአዴግ ለዲሞክራሲ የቆመ ተራማጅ ድርጅት ነው” ሊሉ ይችላሉ። ይችን አብራ የተያያዘቸውን ማስታወቂይ እንዲያነቡ እናበረታታለን።

ይህ አሁን በኢትዮጵያ ያለው ዳግማዊ ደርግ (ምናልባትም በአንዳንድ መስፈርት ከደርግ የባሰ ድርጅት ) በቃ ሊባል ይገባዋል። በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን፣ ሁላችንም በተገኘው መድረክ ሁሉ ድምጻችንን ማሰማት አለብን።

ይሄንንም ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እንዲረዳ፣ በመስከረም 2007 ዓ.ም ፣ በአዲስ አበባ ወጣቶች አነሳሽነትና ግፊት፣ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተዘጋጅቷል። እያንዳንዳችን በአገራችን መብታችንን ለማስከበር እንነሳ። ድምጻችንን እናሰማ። እነርሱ ፣ መብታችንን የሚረግጡት፣ የሽብርተኛ ሕግ እያሉ የሚያሸብሩት፣ በአገራችን ባሪያና መጫወቻ የሚያደርጉት ጥቂቶች ናቸው። እኛ ሚሊዮኖች ነን።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1809

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>